Nile vet. Clinic

Nile vet. Clinic Veterinary services እንስሳትን መንከባከብ ሰብዓዊነት ነው!
(1)

08/11/2023
አስተያየት ስጡበት እሥኪ
31/07/2023

አስተያየት ስጡበት እሥኪ

በምስራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በአገረ ሰላም ቀበሌ የእብድ ውሻ በሽታን (Rabies) 'ን ለመከላከል የውሻ እና የድመት ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።       የአገረ ሰላም ቀበ...
28/07/2023

በምስራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በአገረ ሰላም ቀበሌ የእብድ ውሻ በሽታን (Rabies) 'ን ለመከላከል የውሻ እና የድመት ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።
የአገረ ሰላም ቀበሌ የእንስሳት ጤና ባለሙያ አቶ ይታያል ታደሠ እንደገለፁት "የእብድ ውሻ በሽታ በአሁኑ ወቅት ለቀበሌያችን አሳሳቢ በሚባል ደረጃ ላይ ባይገኝም አልፎ አልፎ የውሾች ድንገተኛ ሞት መከሰት ክትባቱን እንድንሰጥ አድርጎናል። ስለሆነም ቫይረሱን በዋናነት የሚያስተላልፉ የቤት እንስሳትን (ውሻ እና ድመትን) ክትባት በመስጠት በሽታውን ለመከላከል ጥረት እያደረግን እንገኛለን" ብለዋል።
የእብድ ውሻ በሽታ በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በመከሰት የሰው ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን ከወረዳው ጤና ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለእንስሳት ሐኪሞች ፣ ለረዳት እንስሳት ሐኪሞች ፣ ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች እንዲሑም እና አጠቃላይ ለእንስሳት አፍቃሪዎች በሙሉ እና ለዚሕ ፔጅ ቤተሠቦች በሙሉ የእነናንተን እርዳታ እንፈልጋ...
04/07/2023

ለእንስሳት ሐኪሞች ፣ ለረዳት እንስሳት ሐኪሞች ፣ ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች እንዲሑም እና አጠቃላይ ለእንስሳት አፍቃሪዎች በሙሉ እና ለዚሕ ፔጅ ቤተሠቦች በሙሉ የእነናንተን እርዳታ እንፈልጋለን ።
ለእናንተ 1 ደቂቃ ነው የሚፈጅባችሑ ለእኛ ደግሞ ሙያችን ተደራሽ እንዲሆንልን ትልቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ታበረክቱልናላችሑ ይሕን ሊንክ በመጫን ቲክቶክ ፎሎው እና ሼር እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን https://www.tiktok.com/?_t=8dhToRJK7yn&_r=1 ቢያንስ 10K መግባት አለብን ይሔ የሚሆን ደግሞ በእናንተ እርዳታ ነው።
እናመሠግናለን

መልእክትየእብድ ውሻ በሽታሬቢስ በሽታ ምንድን ነው?- በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ...
02/07/2023

መልእክት

የእብድ ውሻ በሽታ
ሬቢስ በሽታ ምንድን ነው?

- በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ ነው።
- የእብድ ውሻ በሽታ የተባለበት ምክንያት በአበዛኛው የቫይረሱ ተሸካሚዎች በአካባቢያችን የሚገኙ ውሾች በመሆናቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የለሊት ወፍ ፣ ፈረስ ፣ ላም ፣ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ከዉሻ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሬቢስ በሽታ በአብዛኛው ታዳጊ ሀገራትን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ህጻናት ለጆችን ስለበሽታው እና ከትባቱ በቂ ግንዛቤ በሌላቸው የሀገራችን ክፍሎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።

መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
- በቫይረሱ ከተጠቁ እንስሳት በተለይ ከውሾች ወደ የሰው ልጅ በንክሻ ወይም በመቧጨር ከአፉቸው በሚወጣ ፈሳሽ (saliva) በቀጥታ ቆዳን ዘልቆ የሚገባ ከሆነ ወይም በሰወነታችን ትኩስ ቁስል (fresh skin wounds) ካለ ሊተላለፍ ይችላል።
- በተለይ የተነከስነው ወይም የተቧጨርነው አንገት እነ ከአንገት በላይ ከሆነ ቫየረሱ በፍጥነት ወደ ማእከላዊ የነርቭ ስርአት (central nervous system) ቅርብ ስለሆነ በፍጥነት ወደ አንጎል (brain) በመድረስ ለሞት ሊዳርገን ይችላል።
- የሬቢስ በሽታ theroetically ከቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ወደ ሰው በንክሻ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል።

ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

-አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጋለጠ በኃላ ምልክት እስከሚያሳይ (incubation period) ከ3ሳምንት እስከ 3 ወር ሊቆይ ይችላል።
- ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች የተነከሰበት ቦታ ለይ መጠዝጠዝ አና መደንዘዝ ፣ ትኩሳት ፣ እራስ ምታት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ጡንቻ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ ፍራቻ ፣ ከመጠን በላይ ምራቅ መኖር ፣ ለመዋጥ መቸገር ፣ ቅዠት ፣ ግራ መጋባት ፣ ዉሃን መፍራት (hydrophobia) ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ የከፉ ደረጃ ሲደርስም ለኮማ ከዛም ለሞት ሊዳረግ ይችላል።
- ምልክቶቹን ማሳየት የጀመረ ሰው የመዳን አድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።

እንዴት መከላከል እንችላለን?

- የቤትም ሆነ የዱር እንስሳ ካለን ማስከተብ
-ሌላው መርሳት የሌለብን ነገር ክትባቱን ባልተከተቡ እንስሳት ከተነክሰን ወይም ጥርጣሬ እንኳን ቢኖርብን ግዜ ሳንሰጥ ወዲያውኑ የህክምና ባለሙያ በማማከር የተጋላጭነት ክትባቱን (post exposure prohpylaxis) መዉሰድ አለብን።

ህክምናውስ?

- የሬቢስ በሽታ ይሄ ነው ሚባል ህክምና የለውም። ምክነያቱም የሬቢስ ቫይረስ ሰውታችን ውስጥ ከገባ እራሱን ስለሚደብቅ በጸረ ቫይረስ (Anti viral) አንኳን መዳን አይችልም።
- ስለዚህ ማንኛውም አይነት ቁስል በሰውነታችን ለይ ካለ በአግባቡ መታከም እና ተጋላጭ ከሆንን ጊዜ ሳነሰጥ የህክምና ቦታ በመሄድ ከትባቱን መከተብ ብቸኛ አማራጮች ናቸው።
- በአጠቃላይ የሬቢስ በሽታ ችላ የማይባል ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ በመሆኑ ሁሉም ከውሻ በሽታ መጠበቅ ይገባል።

በቅሎ ይወልዳል ወይ? በቅሎ ከወንድ አህያ እና ከሴት ፈረስ ልትፈጠር እንደቻለች ሁላችንም እንገነዘባለን። አህዮች 62 ክሮሞዞም ያላቸው ሲሆን በአንፃሩ ፈረሶች 64 ክሮሞዞም አላቸው። 64 ክ...
29/05/2023

በቅሎ ይወልዳል ወይ?

በቅሎ ከወንድ አህያ እና ከሴት ፈረስ ልትፈጠር እንደቻለች ሁላችንም እንገነዘባለን። አህዮች 62 ክሮሞዞም ያላቸው ሲሆን በአንፃሩ ፈረሶች 64 ክሮሞዞም አላቸው።

64 ክሮሞዞም (ፈረስ) + 62 ክሮሞዞም (አህያ) = 32 ክሮሞዞም ከፈረስ እና 31 ክሮሞዞም ከአህያ ጥንድ በመያዝ በድምሩ 63 ክሮሞዞምን በመያዝ በቅሎ ሊፈጠር እንደቻለ የዘርፉ ሳይንስ ያስቀምጣል።

በቅሎ 63 ክሮሞዞምን ይዛ ደግሞ ሌላ ፍጡር ልትፈጥር እንደማትችል እንዲሁ ተጠቅሷል። ለምን በቅሎ ልትወልድ አትችልም?

በተለምዶ የሴክስ ሴል ለመራባት እኩል ቅጥሮችን በመያዝ ሊሆን እንደሚገባው ከኛው ከሰው ልጆች እንማራለን 23 ከአባት 23 ከእናት ይሆንና እኩል ቁጥር 46 የተሳካ የሴክስ ሴል ብዜት (ሚዮሲስ ዲቪዥንን) ሊካሄድ ይችላል።

ነገር ግን የተፈጠሩ በቅሎዎች በሚኖራቸው ተጨማሪ አንድ ክሮሞዞም ምክንያት ይህን ሊያካሂድ አይችሉም ምክንያቱም የሚዮሲስ ዲቪዥን (የሴክስ ሴል ብዜት) ይፈጠር ዘንድ እኩል ቁጥር ያላቸው የወንድና የሴት ክሮሞዞሞች ፔር (ሆሞሎገስ የሆኑ) ማድረግ መቻል አለባቸው።

በቅሎ ጋር ስንመጣ ግን ይህ እኩል ቅጥር (Even No.) የለም። ምንክንያቱም 31 ከአህያ አባት እና 32 ከእናት ፈረስ ተደምረው እኩል ያልሆነ ቁጥር 63 ስለሚሆን (Odd)። ይህን ደግሞ ፔር ማድረግ አይችልም፣ ፔር(ማች) ማድረግ ካልቻለ ደግሞ የተሳካ የሴክስ ሴል ብዜት (ሚዮሲስ ዲዥን) ማካሄድ አይቻልም። በዚህም ምክንያት በቅሎ ልቶልድ አትችልም ማለት ነው።

ይህ ሲሆን ግን የተለ አጋጣሚ(Exceptional) የለም ማለት ግን አይደለም። ምናልባት በቅሎ እኩል ቁጥር ያላቸው የሴት ዘር በአጋጣሚ ካገኘችና ከእኩል ቅጥር ካለር የወንድ ዘር ጋር ፔር ማድረግ ከተቻለ ከስንት አንዴ አህያ የሚመስል ፈረስ ወይም ፈረስ የሚመስል አህያ ልቶልድ እንደምችል ጥቂት የማይባሉ ጥናቶች ያሳያል።

በ ዶ/ር ይመስገን ታረቀኝ

22/05/2023

በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ሳይንስ እና ህክምና ኮሌጅ መምህር የሆነው ዶ/ር ንጉስ አበበ በሀገረ ቻይና የፒ.ኤች.ዲ ዲግሪውን አጠናቋል።

ዶ/ር ንጉስ አበበ በቀድሞ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እጅግ የሚወደድ እና ምስጉን መምህር ነው። ለወንድማችን እና መምህራችን ዶ/ር ንጉስ አበበ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እንወዳለን።

Via: ዶ/ር ሳላሀዲን አሊ
ከተማሪነት በላይ ለለውጥ

እውነታ!
19/04/2023

እውነታ!

ለቅርጫ ካረዱት በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ያገኙት ዕድለኞች ******************* በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎ...
18/04/2023

ለቅርጫ ካረዱት በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ያገኙት ዕድለኞች
*******************

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል።

በሬውን በ40 ሺህ ብር የገዙት ተቃራጮቹ፣ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺህ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺህ ብር ማትረፍ ችለዋል።

ነገር ግን ተቃራጮቹ ሌላ በሬ ለመግዛት ወስነዋል፤ የተቃራጮቹ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በቀለ ቀነኒ እንዳሉት፣ ከወርቁ ሽያጭ በተገኘው ገንዘብ ሌላ በሬ ለመግዛት ቀጠሮ ይዘዋል።

ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ፣ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

በሀገራችን በዓላት በመጡ ቁጥር ቅርጫ መቃረጥ የተለመደ እና የአብሮነት መገለጫችን ከሆኑት እሴቶች አንዱ ነው።

ማሕበራዊ ኑሮከቅርብ አመታት ወዲሕ በሐገራችን የተፈጠረው እና እየተካሔደ ያለው ማሕበራዊ ፖለቲካዊ እና መንፈሣዊ ክሥተቶች ሐገራችን ኢትዮጵያን "ከድጡ ወደማጡ እና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ...
10/04/2023

ማሕበራዊ ኑሮ

ከቅርብ አመታት ወዲሕ በሐገራችን የተፈጠረው እና እየተካሔደ ያለው ማሕበራዊ ፖለቲካዊ እና መንፈሣዊ ክሥተቶች ሐገራችን ኢትዮጵያን "ከድጡ ወደማጡ እና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " አይነት ሐገር በቀል አባባሎችን በተግባር እንድናያቸው እና እንድንለማመዳቸው በር ከፍቶልናል።

በኢትዮጵያ ምድር አንዱን መከራ ሥናልፈው ከአየነው የበለጠ ግዙፍ መከራ እየተፈጠረ የወገኖቻችንን ነፍሥ ያለእድሜአችው እየቀጠፈ አለፍ ሢልም በተወለዱበት ሐገር እንደጠላት እየተቆጠሩ ያፈሩትን ሐብትና ንብረት እየተዘረፈ የተቀረውም እየተቃጠለ ከተመለከትን በርካታ አመታቶችን ብናሥቆጥርም ያለፉት 5 አመታት ግን ሐገራችን ኢትዮጵያ #በዱርየ መንግሥት እንደምትመራ ያሥመሠከረ በርካታ አፀያፊ እና አሠቃቂ አበይት ጉዳዮችን በአይናችን አሥተውለናል።

እኛም ከዛሬ ነገ የተሻለ ሕይወት ሊመጣ ይችላል እያልን በትግሥት ነገሮችን ሥናሣልፍ ብንቆይም አሑን ግን ሑሉም ነገር ከአቅማችን በላይ ከመሆኑ አልፎ ለሕይወታችን አሥጊ ደረጃ ላይ ደርሠናል።

የእንሥሣት ሕክምና ሙያ 99% ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በቀጥታ ይገናኛል ያ ማለት አንድ የእንሥሣት ሐኪም ሥራ አቆመ ማለት በቀን የ1000 ሕዝብ ኑሮ ይመሠቃቀላል በተዘዋዋሪም የሐገሪቱ ኢኮኖሚ 75% የዋጋ ግሽበት ያጋጥመዋል ማለት ነው።

ሥለዚሕ እኛ ምን እናድርግ?
በቅርብ ቀን ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን!

ሠላም በሠው ልጆች ግብር ይከፈላል!

ቦረናሐገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲሕ በሠው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ድርቅ በእርስ በእርስ ጦርነት በፖለቲካ ጡዘት በሐይማኖት ግጭት በሤራ ፖለቲካ ተጠምዳ አጣብቂኝ ማጥ ውስጥ ከገባች ዋል...
23/02/2023

ቦረና

ሐገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲሕ በሠው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ድርቅ በእርስ በእርስ ጦርነት በፖለቲካ ጡዘት በሐይማኖት ግጭት በሤራ ፖለቲካ ተጠምዳ አጣብቂኝ ማጥ ውስጥ ከገባች ዋል አደር ብላለች፤ ስርዓተመንግስቷ መደበኛ ሥራውን ወደጎን በማለት በብሔር ካባ ሥር ተጀቡኖ እንደ መንግስት ሣይሆን ከብሔርተኞች እንደአንዱ በመሆን በመሆን መስራት የሚገባውን ወደጎን በማለት ከዘረኞች እና ግጭት ጠማቂዎች ጋር በመወገን ጀርባ ለጀርባ ሢተሻሽ ይውላል።
በዚሕ ሑሉ መሐል የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በርሐብና በሥደት ሕይወቱ በአጭር እየተቀጨ እያስተዋልን ነው መረጀዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ደግሞ ከ 30 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ የሚያሥፈልገው ሆኖ ተገኝቷል። የቦረና ሕዝብ ደግሞ አስከፊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ሕይወት አድን እርዳታ በአስቸኳይ እንዲደርሠው የበኩላችንን ጥረት ልንወጣ ይገባል ፤ መንግስትም ጉዳዩን ከማደባበስ እና ከማለባበሥ ወጥቶ የተፈጠረውን ችግር በቅርበት በማየት የእርዳታ ማሰባሠቢያ እና ገቢ ማሥገኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለተጎዱ ወገኖቻችን እንዲደርስ በአስቸኳይ እንጠይቃለን።

 #አስገራሚ ክስተትበምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በሰላም አበበ ቀበሌ አንዲት በግ 8 እግርና 4 ጆሮ ያላት ግልገል የተወለደች ሲሆን ግልገሏ እስከዛሬ ከታየው የተለየ አወላለድ ...
08/02/2023

#አስገራሚ ክስተት
በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በሰላም አበበ ቀበሌ አንዲት በግ 8 እግርና 4 ጆሮ ያላት ግልገል የተወለደች ሲሆን ግልገሏ እስከዛሬ ከታየው የተለየ አወላለድ ስለሆነ ወዲያውኑ መሞቷን የቀበሌው የእንስሳት ሀኪም ገልፆል።
ምንጮ:- ጎንቻ ሢሦ እነሤ ወረዳ

ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ!
27/01/2023

ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ!

እንኳን ጥምቀት በዓል አደረሣችሑ አደረሠን!
19/01/2023

እንኳን ጥምቀት በዓል አደረሣችሑ አደረሠን!

ክፍት የስራ ማስታወቅያቦንጋ ዩኒቨርስቲ የስራ አይነት: ሌክቸርየትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)የትምህርት ደረጃ: MSc Vet. Clinical medicine የስራ ልምድ: 0 እ...
20/11/2022

ክፍት የስራ ማስታወቅያ
ቦንጋ ዩኒቨርስቲ

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc Vet. Clinical medicine
የስራ ልምድ: 0 እና ከዛ በላይ
ተፈላጊ ብዛት: 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. ፐብሊክ ሄልዝ
የስራ ልምድ:0 እና ከዛ በላይ
ተፈላጊ ብዛት: 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. Immunology
የስራ ልምድ: 0 እና ከዛ በላይ
ተፈላጊ ብዛት: 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. Histology
የስራ ልምድ: 0 አመት
ብዛት፡ 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. Surgery
የስራ ልምድ: 0 እና ከዛ በላይ
ብዛት፡ 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል
የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. Pharmacology
የስራ ልምድ: 0 እና ከዛ በላይ
ብዛት፡ 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. parasitology
የስራ ልምድ:0 እና ከዛ በላይ
ብዛት፡ 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. Anatomy
የስራ ልምድ: 0 እና ከዛ በላይ
ብዛት፡ 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የስራ አይነት: ሌክቸር
የትምህርት አይነት: የእንስሳት ህክምና (DVM)
የትምህርት ደረጃ: MSc in Vet. Physiology
የስራ ልምድ: 0 እና ከዛ በላይ
ብዛት፡ 1
ቦታ፡ ቦንጋ
ደመወዝ: በዩኒቨርስቲ ስኬል

የምዝገባ ቦታ
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ (0474524527)
አዲስአበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት የሚገኘው የዩኒቨርስቲው ወኪል ቢሮ በአካል በመቅረብ (0111261752)

በእንስሳት ሐብት ዘርፍ ኢትዮጵያን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ተግባር ሥለሆነ በርቱልን ውድ የሙያ ወንድሞቻችን!
04/11/2022

በእንስሳት ሐብት ዘርፍ ኢትዮጵያን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ተግባር ሥለሆነ በርቱልን ውድ የሙያ ወንድሞቻችን!

09/09/2022

maltese puppies

abyu shibabawበ፪እጁ እነሴ ወረዳ እስሳትና አሳሀብት ልማት ፅፈትቤት በገዳማዊት ቀበሌ እስሳት ክሊኒክ የበጎችና ፈየሎች ደስታመሰል \PPR)በሽታ የክትባት ዘመቻ በቀን05\12\2014 ...
11/08/2022

abyu shibabaw

በ፪እጁ እነሴ ወረዳ እስሳትና አሳሀብት ልማት ፅፈትቤት በገዳማዊት ቀበሌ እስሳት ክሊኒክ የበጎችና ፈየሎች ደስታመሰል \PPR)በሽታ የክትባት ዘመቻ በቀን05\12\2014 በዚህ መልኩ ተጀምሮአል።

እሥከመቼ በየግል እንጠይቅ?ፌደራል የሚሠሩት ለብቻቸው ክልል ላይ የሚሠሩት ለብቻቸው ዞንና ወረዳ ላይ የሚሠሩት እንስሳት ሐኪሞችም ለብቻቸው የራሣቸውን ጥቅም ሢያሣድዱ ቀበሌ ላይ 24/7 ደከመ...
29/07/2022

እሥከመቼ በየግል እንጠይቅ?
ፌደራል የሚሠሩት ለብቻቸው ክልል ላይ የሚሠሩት ለብቻቸው ዞንና ወረዳ ላይ የሚሠሩት እንስሳት ሐኪሞችም ለብቻቸው የራሣቸውን ጥቅም ሢያሣድዱ ቀበሌ ላይ 24/7 ደከመኝ ሠለቸኝ ሣይሉ ምሥኪኑን ገበሬ የሚያገለግሉት ከወረዳ ቀበሌ ረጅም የእግር መንገዶችን ተጉዘው የእንሥሣት መድሐኒት በትክሻቸው ተሸክመው የሕብረተሠቡ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉት የእንሥሣት ጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ አንድም ጊዜ በአጀንዳ ደረጃ ተይዞላቸው አያቅም።
ለምን ?
ኢትዮጵያ ሐገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የደከመልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።

ቀበሌ ላይ የምትሠሩ እንሥሣት ባለሙያዎች ይሔን ነገር አሥቡበት።
ሠላማዊ ሠልፍ ለማዘጋጀትም ቅድመ ዝግጅት እናደርጋለን።

እድላችሑን ሞክሩ!
29/06/2022

እድላችሑን ሞክሩ!

03/06/2022
እርስዎ ምን ይፈልጋሉ?በአቅራቢያዎ የሚገኝ የእንስሳት ሐኪም   እንዲሑም ለሚፈልጉት ማነኛውም አገልግሎት በ ቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/nileanimalclinic join በማድረ...
22/02/2022

እርስዎ ምን ይፈልጋሉ?

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የእንስሳት ሐኪም እንዲሑም ለሚፈልጉት ማነኛውም አገልግሎት በ ቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/nileanimalclinic join በማድረግ እና በቲክ ቶክ tiktok.com/
ቤተሠብ ይሑኑን ጥያቄዎችን መጠየቅ እና አገልግሎቱን ማግኘት ትችላላችሁ ።
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ይካቲት 15 - 2014

ሠላም ሠላም እንዴት ናችሑ ውድ ኢትዮጵያውያን እነሆ ዛሬም እንደተለመደው ከጀርመን ሐገር የመጡ የ 2 ወር real  German Shepherd  ቡችሎች ለሽያጭ አቅርበናል መግዛት የምትፈልጉ በ...
08/02/2022

ሠላም ሠላም እንዴት ናችሑ ውድ ኢትዮጵያውያን እነሆ ዛሬም እንደተለመደው ከጀርመን ሐገር የመጡ የ 2 ወር real German Shepherd ቡችሎች ለሽያጭ አቅርበናል መግዛት የምትፈልጉ በ 09 66 30 00 00 ማነጋገር ትችላላችሑ።
ሙሉ ክትባት እና የ ፓራሣይት የተሠጡ ።
ዋጋቸው 13,000 ብር!
አዲስአበባ !
ኢትዮጵያ !

06/02/2022

How to train any dogs?

ሰላም ውድ የእንስሳት ሐኪሞች ቤት ቤተሰቦች አገልግሎታችንን በአዲሥ መልክ እና በጥራት ለመሥራት ያመቸን ዘንድ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሠናል እንደተለመደው የእናንተን መልካም ትብብር እንጠይቃለን የሚቀጥለውን የዩቲዩብ ሊንክ https://youtube.com/channel/UCPnez1ci-ieZ3_htY7-xrwg ሰብስክራይብ ብታደርጉ የተለያዩ የቤት እንስሳዎችን ማለትም ውሻ እና ድመት እንዴት ማሠልጠን እና ማዘዝ እንደምንችል ሠፊ ትምህርት ማግኘት ትችላላችሑ በተጨማሪም የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/nileanimalclinic join ብታደርጉ በተለያዩ የሐገራችን ክፍሎች የሚገኙ ረጂም የሥራ ልምድ ያላቸውን የእንስሳት ሐኪሞችን ማግኘት ትችላላችሑ!
እናመሠግናለን !

ሰላም ውድ የእንስሳት ሐኪሞች ቤት ቤተሰቦች አገልግሎታችንን በአዲሥ መልክ እና በጥራት ለመሥራት ያመቸን ዘንድ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሠናል እንደተለመደው የእናን...
05/02/2022

ሰላም ውድ የእንስሳት ሐኪሞች ቤት ቤተሰቦች አገልግሎታችንን በአዲሥ መልክ እና በጥራት ለመሥራት ያመቸን ዘንድ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሠናል እንደተለመደው የእናንተን መልካም ትብብር እንጠይቃለን የሚቀጥለውን የዩቲዩብ ሊንክ https://youtube.com/channel/UCPnez1ci-ieZ3_htY7-xrwg ሰብስክራይብ ብታደርጉ የተለያዩ የቤት እንስሳዎችን ማለትም ውሻ እና ድመት እንዴት ማሠልጠን እና ማዘዝ እንደምንችል ሠፊ ትምህርት ማግኘት ትችላላችሑ በተጨማሪም የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/nileanimalclinic join ብታደርጉ በተለያዩ የሐገራችን ክፍሎች የሚገኙ ረጂም የሥራ ልምድ ያላቸውን የእንስሳት ሐኪሞችን ማግኘት ትችላላችሑ!
እናመሠግናለን !

ስጦታየ9ወር ሙሉ ክትባት የተከተበች ለማዳ የቤት ውሻ በነፃ መውሠድ የሚፈልግ ሰው በ 0920958136 ደውሎ መውሠድ ይችላል።አድራሻ:- አዲስአበባ ኢትዮጵያ!
22/01/2022

ስጦታ

የ9ወር ሙሉ ክትባት የተከተበች ለማዳ የቤት ውሻ በነፃ መውሠድ የሚፈልግ ሰው በ 0920958136 ደውሎ መውሠድ ይችላል።
አድራሻ:- አዲስአበባ
ኢትዮጵያ!

እባካችሑ አፋልጉኝ!
23/12/2021

እባካችሑ አፋልጉኝ!

21/12/2021

Welcome to the White House, Commander.

Address

Addis Ababa
BOLEMEDIHANIALEM

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nile vet. Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Nile vet. Clinic:

Videos

Share

Category