Haramaya University

Haramaya University Haramaya University is one of the oldest universities in Ethiopia. It is located 5 km from Haramaya, welcome

30/06/2025
 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተጀመረሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸው ዛሬ መውሰድ ጀምረዋል።ዛሬ ጠዋት የእንግሊዝኛ...
30/06/2025



የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተጀመረ

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸው ዛሬ መውሰድ ጀምረዋል።

ዛሬ ጠዋት የእንግሊዝኛ ፈተና እየተሰጠ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ የሒሳብ ፈተና ይወስዳሉ።

በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጠን የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲወስዱ ከተመደቡ 7029 ተማሪዎች መካከል 4271 ወንድ እና 2375 ሴት በድምሩ 6646 ተማሪዎች ፈተናቸው እየወሰዱ ነው።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፈተና እንዲወስዱ ከተመደቡ ተፈታኞች 258 ወንድ እና 125 ሴቶች በድምሩ 383 ተፈታኞች ሳይመጡ ቀርተዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ተፈታኞች የፈተናውን መመሪያ በተመለከተ ገለፃ እየተደረገላቸው ነው።የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀ...
29/06/2025



የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ተፈታኞች የፈተናውን መመሪያ በተመለከተ ገለፃ እየተደረገላቸው ነው።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 22/2017 ዓ.ም

 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲፈትኑ ለተመደቡ ፈታኞች ገለፃ እየተደረገላቸው ነው።ከሰዓት በኋላ 7፡30 ጀምሮ ለተፈታኞቹም ገለፃ ይደረጋል።የሐረማ...
29/06/2025



የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲፈትኑ ለተመደቡ ፈታኞች ገለፃ እየተደረገላቸው ነው።

ከሰዓት በኋላ 7፡30 ጀምሮ ለተፈታኞቹም ገለፃ ይደረጋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 22/2017 ዓ.ም

Haramaya University Hosts a Workshop on Oromia's Agricultural Technology FutureHaramaya University (HU), in collaboratio...
28/06/2025

Haramaya University Hosts a Workshop on Oromia's Agricultural Technology Future

Haramaya University (HU), in collaboration with the Oromia Science and Technology Authority, hosted a workshop on "Oromia Regional Agricultural Technology Needs Assessment, Utilization, and Roadmap Development."

The event, held at the university's Resource Center, brought together key stakeholders to strategize on enhancing agricultural development and food security in the Oromia region.

The workshop underscored Haramaya University's significant role in advancing Ethiopia's agricultural sector. Dr. Ketema Bekele, delegate of the Vice President for Administration and Development at Haramaya University, highlighted the university's commitment to technology needs assessment research, particularly in mechanization, and its crucial role in providing strategic direction for such development initiatives.

Mr. Kemal Qasim, Director of Community Engagement and Industry Linkage at Haramaya University, articulated the workshop's core objective: to develop a comprehensive roadmap for sustainable agricultural growth in Oromia. He emphasized the importance of transforming agriculture through improved policies and guidelines tailored to societal needs and technological advancements.

This initiative, Mr. Kemal explained, is part of a broader effort involving national and international agricultural research centers to drive technological implementation and development in the country.

Dr. Dinaol Balina, an academic staff member at Haramaya University, elaborated on the project's origins, noting that the Oromia Science and Technology Authority initiated the concept. The study, conducted by the Office of the Vice President for Research and Community Development at Haramaya University, thoroughly assessed gaps, opportunities, and the current state of agricultural technologies in Oromia.

Dr. Beyan Ahmed, a lecturer and Project Team Leader at HU, highlighted the practical benefits of their study. He noted its significance for regional research centers, government policymakers, and other relevant stakeholders, including future university research. He emphasized that the study's findings, through the development of agricultural technologies and innovations, will play a crucial role in ensuring food security and fostering sustainable agricultural development for national economic growth.

The findings from various regional studies will inform the preparation of a roadmap for agricultural activities, encompassing both crop and animal husbandry technologies, with the aim of improving regional policies.

Dr. Lijalem Ayele, Deputy Director General of the Oromia Science and Technology Authority, commended Haramaya University for its substantial contributions to Ethiopia's agricultural sector, recognizing it as a cornerstone of the national economy. He stressed the authority's collaboration with HU to broaden access to technology and boost research and development efforts across the Oromia region.

Dr. Lijalem emphasized the need to assess technology implementation gaps in such a vast region and highlighted that the study presented at the workshop was a direct result of a request made to Haramaya University a year prior to address these critical needs.

The workshop saw active participation from representatives of the Oromia Science and Technology Authority, the Oromia Agriculture Office, and other relevant stakeholders, including Haramaya University researchers.

Discussions during the event reinforced the critical importance of collaborative research and practical implementation by all stakeholders for the sustained agricultural development of the region.

Reporter: Shemsedin Mohammed Photographer: Fuad Ahmed
Haramaya University Public and International Relations Directorate

የትምህርት ፕሮግራሞች ጊዜውን የዋጁና የገበያውን ፍላጎት ያማከሉ መሆን እንደሚገባቸው ተገለጸየሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሁለት በቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሀግብሮች ላይ የ...
27/06/2025

የትምህርት ፕሮግራሞች ጊዜውን የዋጁና የገበያውን ፍላጎት ያማከሉ መሆን እንደሚገባቸው ተገለጸ

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሁለት በቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሀግብሮች ላይ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሂዷል።

በቅድመ ምረቃ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት አዲስ መርሀ ግብርናና በድህረ-ምረቃ ደግሞ ማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ነባር ስርዓተ-ትምህርት ላይ የውጭ ግምገማ ያካሄደው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ተባባሪ ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ይማም በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ከመለየቱና ወደፊትም ራስ-ገዝ ለመሆን በሂደት ላይ ስለሚገኝ የቅድመ-ምረቃም ሆነ ድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን ዓለም የደረሰበትን ነባራዊ ሁኔታ ፣ የባለድርሻና የተማሪዎች ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ መከለስና አዳዲስ ፕሮግራሞችም መቅረጽ ይገባል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲው በምስራቅ አፍሪካ ተፈላጊነት ያላቸው ፕሮግራሞችን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስርዓተ-ትምህርቶች በተወሰን ጊዜ ውስጥ መከለስ የሚገባቸው ስለሆነና እንደ አስፈላጊነቱ አዳዲስ ፕሮግራሞችን መክፈት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ አዲስ የሚከፈተውን ፕሮግራም በተመለከተ የፍላጎት ዳሰሳ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በማካሄድና ነባር ፕሮግራሙን ጊዜውን ያማከለ ለማድረግ ስርዓተ ትምህርት ግምገማው መካሄዱን የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን አቶ አራርሳ አበራ ገልጸዋል፡፡

የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ያስሚን መሃመድ በበኩላቸው ስርዓተ-ትምህርቶች ሲከለሱ በፕሮግራሙ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች ለመሙላትና በጊዜ ሂደት ውስጥ መጨመርና መቀነስ ያለባቸውን ጉዳዮችን ለማስተካከል እድል ይሰጣል፡፡ ከውጭ ገምጋሚዎችም ጥሩ ግብዓቶች ስለተገኙ እሱን በማካተት ወደቀጣይ ደረጃ የሚያልፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

በስርዓተ-ትምህርት ግምገማ መድረኩ ላይ ባለድርሻ አካላት ፣ ተጋባዥ እንግዶችና የኮሌጁ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘጋቢ፦ አወቀ አያልነህ
ፎቶግራፈር፦ ቴዎድሮስ ሊሻን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 2017 ዓ.ም

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ አካሄደ ክለሳው ከዚህ በፊት በሁለተኛ ዲግሪ ሲሰጡ በነበሩ የስፖርት ሳይንስ ሜዲሲንና የስፖርት ሳይንስ ኒውትሪሽን ትምህር...
27/06/2025

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ አካሄደ

ክለሳው ከዚህ በፊት በሁለተኛ ዲግሪ ሲሰጡ በነበሩ የስፖርት ሳይንስ ሜዲሲንና የስፖርት ሳይንስ ኒውትሪሽን ትምህርት አይነቶች ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ታስቦ መሆኑ ታውቋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው አበበ እንዳብራሩት ስርዓተ ትምህርት አሁን ያለውን ሳይንሳዊ አረዳድ የሚያንፀባርቅ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ተለዋዋጭ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን የማዘጋጀት ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ ዲን ዶክተር ደስታ እንየው እንዳሉት ፕሮግራሞች ከዚህ በፊት የውስጥ ክለሳ የተደረገበትና አሁን ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ የክለሳ ግምገማ እንደተካሄደበት በስፖርት ሜዲስን ከጂማ ፣ ከድሬዳዋ ፣ ከወሎና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገምጋሚዎች እንደተሳተፉበት ገልፀዋል።

የገበያውን ፍላጎት በማየትና ጥናታዊ ዳሰሳዎችን በማድረግ አዋጭ መሆኑ ስለታወቀ የትምህርት ክለሳ መደረጉን የተናገሩት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊና የስፖርት ህክምና የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡት መምህር ሱፊያን ናቸው።

ተሳታፊ ከነበሩት የውጪ ገምጋሚዎች አንዱ የሆኑትና ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ዶክተር ሳሙኤል አዲሱ በበኩላቸው ከስም ጀምሮ ማሻሻያዎችን ነጥብ በነጥብ በማየት መሰረታዊ ክለሳ መደረጉን ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፦ ሀብታሙ ኃብተጊዮርጊስ ወልደጊዮርጊስ
ፍቶ ግራፍ ፦ ቴድሮስ ሊሻን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 2017 ዓ/ም

  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲፈተኑ የተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ።ፎቶግራፈር፦ ቴዎድሮስ ሊሻንየሐረማያ...
27/06/2025




የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲፈተኑ የተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ።

ፎቶግራፈር፦ ቴዎድሮስ ሊሻን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የአካባቢውን ወጣቶች በስፖርት ፕሮጀክት ስልጠና ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለፀ አካዳሚውን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ለማስገባት ከኢትዮጵያ ስ...
25/06/2025

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የአካባቢውን ወጣቶች በስፖርት ፕሮጀክት ስልጠና ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለፀ

አካዳሚውን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ለማስገባት ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖችና የዩኒቨርቲዎች ስፖርት ማህበር ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ በቀረቡ ጥናታዊ ፅሑፎች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የዩኒቨርሲቲውን ስፖርት አካዳሚ መሰረተ ልማት በመጎብኘትም በጋራ ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ እንዳሉት የትምህርት ተቋማት ለሐገር አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ስፖርተኞች ማፍለቂያ መሆናቸውንና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲም የተሟላ የስፖርት አካዳሚ ያለው በመሆኑ ለሀገር አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባሻገር የገቢ ምንጭ መሆን የሚያስችል አቅም ስላለው የተደረገው ስምምነት ይህንን አቅም ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አባይ በላይሁን እንዳብራሩት የዩኒቨርሲቲዎች ስፖርታዊ ውድድር ተቋርጦ መቆየቱ በዩኒቨርሲቲዎች የስፖርታዊ ውድድሮች መቀዛቀዝ መፍጠሩንና በዩኒቨርሲቲው መሰረተ ልማቶች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ውድድር በ2017 ዓ/ም እንደገና በመጀመሩ መነቃቃትን ካሳዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑን አቶ አባይ ጠቁመው ከተለያዩ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ተወካዮች ጋር በመሆን ዩኒቨርሲቲው ያለውን የመሰረተ ልማትና የሰው ሐይል በማየትና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመወያየት ዩኒቨርሲቲው ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ማፍራት የሚያስችል አቅም እንዳለው ማረጋገጣቸውንና በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል ።

ዩኒቨርሲቲው ያለውን የስፖርት አካዳሚ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ በማስገባት የአካባቢውን ወጣቶች ወደ አካዳሚው በማስገባት በሐገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ዩኒቨርሲቲውን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ መድረኩ መዘጋጀቱን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ ዲን ዶክተር ደስታ እንየው ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፦ ሀብታሙ ኃብተጊዮርጊስ ወልደጊዮርጊስ
ፍቶ ግራፍ ፦ ቴዎድሮስ ሊሻን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 2017 ዓ/ም

Address

Haramaya
Bate
138

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haramaya University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Haramaya University:

Share

Our Story

Well Come To Haramaya University Official page

Historical Background of the University Haramaya University has gone through a series of transformations since its establishment as a higher learning institution. The agreement signed between the Imperial Ethiopian Government and the Government of the United States of America on May 15,1952 laid the foundations for the establishment of Jimma Agricultural and Technical School and the Imperial College of Agricultural and Mechanical Arts (IECAMA). The Agreement between the Government of Ethiopia and the Technical Cooperation Administration of the Government of the United States of America, signed on May 16, 1952, gave the mandate to Oklahoma State University to establish and operate the College, conduct a nationwide system of Agricultural Extension and set up an agricultural research and experimental station. Based on the Emperor’s wish, it was decided to establish the College at its current location at Haramaya. Later on, the agreement signed between the United States Department of States and the Imperial Government provided the basis for the operation of Jimma Agricultural and Technical School that received its first class of eighty students in October 1952. Nineteen of the students graduated on August 6, 1953 and became the first freshman students of the Imperial Ethiopian College of Agricultural and Mechanical Arts (IECAMA). The IECAMA opened its doors to its first batch of students in October 1956 senior class moved from Addis Ababa to Alemaya for their final semester. At the end of the 1956/57 academic year, eleven students completed their studies and graduated with a B.Sc. degree in General Agriculture. The training programs in Agriculture were further specialized and B.Sc. programs were introduced in Animal Sciences (1960), Plant Sciences (1960), Agricultural Engineering (1961) and Agricultural Economics (1962). Until 1963, the college was virtually dependent on Oklahoma State University, both administratively and academically; however, after 1966, when the first Ethiopian dean was appointed, the role of Americans was limited to advisory and technical support. The College became a chartered member of Addis Ababa University (the then Haile Selassie I University), following the contractual termination of Oklahoma State University in 1968. Consequently, it was named Alemaya College of Agriculture. Due to the great need of trained manpower in other areas of study, additional programs that included a diploma program in Home Economics (1967), Science Teachers’ Training Program (1978), and Continuing Education Program (1980) were launched. A major landmark in the history of the College of Agriculture was the launching of graduate study programs in the 1979/80 academic year. This laid the foundation for advanced academic and research work at the institution. When graduate studies were launched, about 29 students were enrolled to study various fields of agriculture. Another major landmark in the history of Alemaya College of Agriculture was when it was upgraded to university status on May 27, 1985, followed by the launching of the Faculty of Forestry in 1987. It was then named Alemaya University of Agriculture that produced qualified manpower in the fields of Animal Sciences, Plant Sciences, Agricultural Economics, Agricultural Engineering, Agricultural Extension and Forestry both at graduate and undergraduate levels. Moreover, in the continuing education program, diploma level training programs were delivered in Accounting and Management, in Dire Dawa and Harar centers. The university once again went through another phase of transformation during the 1995/96 academic year by launching new programs in the fields of Teacher Education and Health. The opening of the two faculties, namely the Faculty of Education and the Faculty of Health Sciences, further diversified the existing programs, and enabled the institution to become a full-fledged university that was renamed Alemaya University (AU). In the last few years, the University has witnessed tremendous expansion in terms of fields of study. In September 2002, two more faculties, namely Faculty of Law and Faculty of Business and Economics, were opened. Furthermore,Faculty of Veterinary Medicine and Faculty of Technology were initiated in 2003 and 2004, respectively to further diversify the training programs of the university. The institution was renamed Haramaya University in February 2006. The University, apart from undergraduate programs, has been highly engaged in the expansion and diversification of graduate programs. .....